ዐሥራቱን በሚቀበሉበት ጊዜም ከአሮን ዘር የተወለደው ካህን ከሌዋውያኑ ጋራ ዐብሮ ይገኛል፤ ሌዋውያኑም የዐሥራቱን አንድ ዐሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት፣ ወደ ዕቃ ማከማቻ ክፍሎች ያመጡታል።
ዘኍል 15:21 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሚቀጥሉት ትውልዶች ሁሉ ከመጀመሪያው ዱቄት ላይ አንሥታችሁ ይህን ቍርባን ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መጀመሪያ ከምታዘጋጁት ሊጥ እንደ ስጦታ አድርጋችሁ የምታቀርቡትን ቁርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለጌታ ትሰጣላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለሚመጡት ዘመናት ሁሉ ከአዲስ እህል ከምትጋግሩት ኅብስት እየተነሣ ለእግዚአብሔር ልዩ መባ ሆኖ መቅረብ አለበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መጀመሪያም ከምታደርጉት ሊጥ የተለየ ቍርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መጀመሪያ ከምታደርጉት ሊጥ የማንሣት ቍርባን እስከ ልጅ ልጃችሁ ለእግዚአብሔር ትሰጣላችሁ። |
ዐሥራቱን በሚቀበሉበት ጊዜም ከአሮን ዘር የተወለደው ካህን ከሌዋውያኑ ጋራ ዐብሮ ይገኛል፤ ሌዋውያኑም የዐሥራቱን አንድ ዐሥረኛ ወደ አምላካችን ቤት፣ ወደ ዕቃ ማከማቻ ክፍሎች ያመጡታል።
ለአሮንና ለወንዶች ልጆቹ የዘወትር የእስራኤላውያን ድርሻ የሚሆነው ይህ ነው፤ ከኅብረት መሥዋዕታቸው እስራኤላውያን ለእግዚአብሔር የሚያቀርቡት ነው።
ከፍሬ በኵራት ምርጥ የሆነው ሁሉ እንዲሁም ከልዩ ስጦታዎቻችሁ የመጀመሪያው ሁሉ ለካህናት ይሆናል፤ ለቤተ ሰዎቻችሁ ሁሉ በረከት እንዲሆን ከምድር የምታገኙትን መብል በኵራት ለእነርሱ ስጧቸው።
ስጦታውን ለአምላካችሁ እስከምታቀርቡበት እስከዚያ ቀን ድረስ፣ እንጀራም ቢሆን ቈሎ ወይም እሸት አትብሉ፤ ይህም በምትኖሩበት ስፍራ ሁሉ ለሚመጡት ትውልዶች የዘላለም ሥርዐት ነው።
“ሌዋውያንን ተናገራቸው፤ እንዲህም በላቸው፤ ‘ርስት አድርጌ የምሰጣችሁን ዐሥራት ከእስራኤላውያን በምትቀበሉበት ጊዜ፣ እናንተም ካገኛችሁት ላይ አንድ ዐሥረኛ በማውጣት ለእግዚአብሔር መባ አድጋችሁ ታቀርባላችሁ።