ዘኍል 10:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት በሰጠው ትእዛዝ መሠረትም ለመጀመሪያ ጊዜ ተጓዙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ በሙሴ አንደበት ባዘዘው መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ተጓዙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እስራኤላውያንም እግዚአብሔር ለሙሴ በሰጠው ትእዛዝ መሠረት ለመጀመሪያ ጊዜ ጒዞ ጀመሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመጀመሪያም እግዚአብሔር በሙሴ ቃል እንዳዘዘ ተጓዙ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመጀመሪያም እግዚአብሔር በሙሴ እጅ እንዳዘዘ ተጓዙ። |
አንዳንድ ጊዜ ደመናው በድንኳኑ ላይ የሚቈየው ለጥቂት ቀን ብቻ ነበር፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍራሉ፤ በእግዚአብሔር ትእዛዝ ጕዞ ይጀምራሉ፤
በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይሰፍራሉ፤ በእግዚአብሔርም ትእዛዝ ይጓዛሉ፤ እነርሱም በሙሴ አማካይነት የተሰጠውን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ ይጠብቁ ነበር።