ማቴዎስ 8:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስ ብዙ ሰዎች በዙሪያው ተሰብስበው ባየ ጊዜ፣ ወደ ባሕሩ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዛቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስ ብዙ ሰዎች በአጠገቡ ሲሰበሰቡ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስ፥ ብዙ ሰዎች በዙሪያው ተሰብስበው ባየ ጊዜ ወደ ባሕሩ ማዶ እንዲሻገሩ ደቀ መዛሙርቱን አዘዘ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢየሱስም ብዙ ሰዎች ሲከቡት አይቶ ወደ ማዶ እንዲሻገሩ አዘዘ። |
ከዕለታቱ በአንድ ቀን፣ ኢየሱስ ከደቀ መዛሙርቱ ጋራ ጀልባ ላይ ወጣ፤ ኢየሱስም፤ “ወደ ባሕሩ ማዶ እንሻገር” አላቸው፤ ከዚያም ጕዞ ቀጠሉ።