ማቴዎስ 19:8 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም እንዲህ አላቸው፤ “ሙሴ የልባችሁን ጥንካሬ አይቶ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ ፈቀደላችሁ እንጂ ከመጀመሪያው እንዲህ አልነበረም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አላቸው “ሙሴ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ የፈቀደላችሁ በልባችሁ ጥንካሬ ምክንያት ነው፤ ከመጀመሪያው ግን እንዲህ አልነበረም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ሙሴማ ሚስቶቻችሁን እንድትፈቱ የፈቀደላችሁ ልባችሁ ደንድኖ አስቸጋሪዎች በመሆናችሁ ምክንያት ነው፤ በመጀመሪያ ግን እንዲህ አልነበረም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም “ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ ሙሴስ ስለ ልባችሁ ጥንካሬ ሚስቶቻችሁን ትፈቱ ዘንድ ፈቀደላችሁ፤ ከጥንት ግን እንዲህ አልነበረም። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “መንታ መንገድ ላይ ቁሙ፣ ተመልከቱም፤ መልካሟን፣ የጥንቷን መንገድ ጠይቁ፤ በርሷም ላይ ሂዱ። ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘በርሷ አንሄድም’ አላችሁ።
ልባቸውን እንደ አልማዝ አጠነከሩ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በቀደሙት ነቢያት በኩል በመንፈሱ የላከውን ቃል ወይም ሕግ አልሰሙም፤ ስለዚህ እግዚአብሔር ጸባኦት እጅግ ተቈጣ።
እላችኋለሁ፤ ዝሙት ፈጽማ እስካልተገኘች ድረስ፣ ሚስቱን ፈትቶ ሌላ ሴት የሚያገባ ሁሉ አመንዝራ ይሆናል፤ እርሷንም አመንዝራ ያደርጋታል፤ የተፈታችውንም ሴት የሚያገባ ያመነዝራል።”
ከዚያም ዐሥራ አንዱ በማእድ ላይ ሳሉ ተገለጠላቸው፤ ከተነሣ በኋላ ያዩት ሰዎች የነገሯቸውን ስላላመኗቸው፣ አለማመናቸውንና የልባቸውን ድንዳኔ ነቀፈ።