ማቴዎስ 15:11 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰውን የሚያረክሰው ከአፉ የሚወጣው እንጂ ወደ አፉ የሚገባው አይደለም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ አፍ የሚገባው ሰውን አያረክሰውም፤ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰውን የሚያረክሰው ከአፍ የሚወጣው ነው እንጂ ወደ አፍ የሚገባው አይደለም!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፤ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው፤” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰውን የሚያረክሰው ወደ አፍ የሚገባ አይደለም፥ ከአፍ የሚወጣው ግን ሰውን የሚያረክሰው ይህ ነው አላቸው። |
የሰደብኸውና ያቃለልኸው ማንን ነው? ድምፅህንስ ከፍ ከፍ ያደረግኸው፣ ዐይንህን በትዕቢት ያነሣኸው በማን ላይ ነው? በእስራኤል ቅዱስ ላይ ነው እኮ!
በጌታ በኢየሱስ ሆኜ በራሱ ንጹሕ ያልሆነ ምንም ምግብ እንደሌለ ተረድቻለሁ፤ ነገር ግን አንድ ሰው አንድን ነገር ንጹሕ እንዳልሆነ የሚቈጥር ከሆነ፣ ያ ነገር ለርሱ ንጹሕ አይደለም።
ለምግብ ስትል የእግዚአብሔርን ሥራ አታፍርስ። ሁሉ ንጹሕ ነው፤ ነገር ግን ለሌላው ሰው የመሰናከያ ምክንያት የሚሆነውን መብላት ስሕተት ነው።
እነርሱ፣ ሰዎች እንዳያገቡ ይከለክላሉ፤ የሚያምኑና እውነትን የሚያውቁ ሰዎች እግዚአብሔር የፈጠረውን፣ በምስጋናም የሚቀበሉትን እንዳይበሉ ያዝዛሉ።
ለንጹሓን ሁሉም ነገር ንጹሕ ነው፤ ለርኩሳንና ለማያምኑ ግን ንጹሕ የሆነ ምንም ነገር የለም፤ እንዲያውም አእምሯቸውና ኅሊናቸው የረከሰ ነው።
በልዩ ልዩ ዐይነት እንግዳ ትምህርቶች አትወሰዱ፤ ልባችን የሚጸናው በጸጋ እንጂ የምግብ ሥርዐት በመጠበቅ አይደለም፤ ይህን ሥርዐት የሚጠብቁት እንኳ በዚህ አልተጠቀሙም።