ማቴዎስ 1:25 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁን እንጂ የበኵር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም፣ “ኢየሱስ” ብሎ ጠራው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የበኩር ልጇን እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁን እንጂ፥ ልጅዋን እስከ ወለደች ድረስ አላወቃትም ስሙንም ኢየሱስ ብሎ ጠራው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበኩር ልጅዋንም እስክትወልድ ድረስ አላወቃትም፤ ስሙንም ኢየሱስ አለው። |
“መጀመሪያ የተወለደውን ወንድ ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ፤ ከእስራኤላውያን መካከል የእናቱ የበኵር ልጅ የሆነው ማሕፀን ከፋች ሰውም ሆነ እንስሳ የእኔ ነው።”
እግዚአብሔር አስቀድሞ ያወቃቸውን የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ወሰናቸው፤ ይኸውም ከብዙ ወንድሞች መካከል እርሱ በኵር እንዲሆን ነው።