ነገር ግን በምድሪቱ ላይ ስለ ተፈጸመው ታምራዊ ምልክት እንዲጠይቁት፣ የባቢሎን ገዦች መልእክተኞችን በላኩ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሊፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ሊያውቅ ስለ ፈለገ ተወው።
ሉቃስ 22:54 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ በኋላ ኢየሱስን ይዘው ወሰዱት፤ ወደ ሊቀ ካህናቱም ግቢ አስገቡት፤ ጴጥሮስም በርቀት ይከተለው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይዘውም ወሰዱት፤ ወደ ሊቀ ካህናት ቤትም አስገቡት፤ ጴጥሮስም በርቀት ይከተለው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሰዎቹ ኢየሱስን ይዘው ወሰዱትና ወደ ካህናት አለቃው ቤት አመጡት፤ ጴጥሮስም ራቅ ብሎ ይከተለው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይዘውም ወደ ሊቀ ካህናቱ ቤት ወሰዱት፤ ጴጥሮስም ከሩቅ ይከተለው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይዘውም ወሰዱት ወደ ሊቀ ካህናት ቤትም አገቡት፤ ጴጥሮስም ርቆ ይከተለው ነበር። |
ነገር ግን በምድሪቱ ላይ ስለ ተፈጸመው ታምራዊ ምልክት እንዲጠይቁት፣ የባቢሎን ገዦች መልእክተኞችን በላኩ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሊፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ሊያውቅ ስለ ፈለገ ተወው።