ሉቃስ 16:30 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እርሱም፣ ‘አብርሃም አባት ሆይ፤ እንደዚህ አይደለም፤ አንድ ሰው ከሙታን ተነሥቶ ቢሄድላቸው ንስሓ ይገባሉ’ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ‘አይደለም፥ አብርሃም አባት ሆይ! ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሓ ይገባሉ፤’ አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሀብታሙም ሰው ‘አይደለም! አባት አብርሃም ሆይ፥ አንድ ሰው ከሞት ተነሥቶ ቢሄድና ቢነግራቸው ግን ተጸጽተው ንስሓ ይገባሉ’ አለ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም፦ ‘የለም፤ አባት አብርሃም ሆይ፥ ከሙታን አንዱ ወደ እነርሱ ካልሄደና ካልነገራቸው ንስሓ አይገቡም’ አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም፦ አይደለም፥ አብርሃም አባት ሆይ፥ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ አለ። |
እርሱም፣ ‘አብርሃም አባት ሆይ፤ ራራልኝ፤ በዚህ ነበልባል እየተሠቃየሁ ስለ ሆነ፣ አልዓዛር የጣቱን ጫፍ ውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያቀዘቅዝልኝ እባክህ ላክልኝ’ እያለ ጮኸ።
እንግዲህ ለንስሓ የሚገባ ፍሬ አፍሩ፤ ደግሞም በልባችሁ፣ ‘አብርሃም አባት አለን’ ማለትን አትጀምሩ፤ እግዚአብሔር ከእነዚህ ድንጋዮች ለአብርሃም ልጆች ማስነሣት እንደሚችል እነግራችኋለሁና።