ሉቃስ 10:10 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ወደ አንድ ከተማ ገብታችሁ ካልተቀበሏችሁ፣ ወደ አደባባዩ ውጡና እንዲህ በሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ወደምትገቡባት ከተማ ሁሉ ባይቀበሉአችሁ፥ ወደ አደባባዮቹዋ ወጥታችሁ እንዲህ በሉ፦ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን በማናቸውም ከተማ ስትገቡ ሰዎቹ የማይቀበሉአችሁ ቢሆን ወደ ከተማይቱ አደባባይ ውጡና እንዲህ በሉአቸው፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ወደ ማናቸውም ከተማ ብትገቡ፥ የዚያች ከተማ ሰዎችም ባይቀበሉአችሁ ወደ አደባባይዋ ወጥታችሁ የእግራችሁን ትቢያ አራግፉ። እንዲህም በሉ፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ወደምትገቡባት ከተማ ሁሉ ባይቀበሉአችሁ፥ ወደ አደባባይዋ ወጥታችሁ፦ |
ማንም ሰው ሊያስተናግዳችሁ ወይም የምትናገሩትን ሊሰማ ፈቃደኛ ካልሆነ፣ ከቤቱ ወይም ከከተማው ስትወጡ የእግሮቻችሁን ትቢያ አራግፋችሁ ውጡ።
‘ለማስጠንቀቂያ እንዲሆናችሁ በእግራችን ላይ ያለውን የከተማችሁን ትቢያ እንኳ እናራግፍላችኋለን፤ ነገር ግን የእግዚአብሔር መንግሥት ቀርባለች ይህን ዕወቁ።’
ነገር ግን በተቃወሙትና በሰደቡት ጊዜ ልብሱን አራግፎ፣ “ደማችሁ በራሳችሁ ላይ ይሁን! እኔ ንጹሕ ነኝ፤ ከእንግዲህ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ” አላቸው።