ዮሐንስ 15:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔን የሚጠላ፣ አባቴንም ይጠላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔን የሚጠላ አባቴን ደግሞ ይጠላል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔን የሚጠላ አባቴንም ይጠላል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔን የሚጠላ አባቴን ይጠላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔን የሚጠላ አባቴን ደግሞ ይጠላል። |
ሌላ ሰው ያላደረገውን በመካከላቸው ባላደርግ ኖሮ፣ ኀጢአት ባልሆነባቸው ነበር፤ አሁን ግን እነዚህን ታምራት አይተዋል፤ ሆኖም እኔንም አባቴንም ጠልተዋል።