አንቺ ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ የተዋብሽ ሆይ፤ የማታውቂ ከሆነ፣ የበጎቹን ዱካ ተከተዪ፤ የፍየል ግልገሎችሽንም፣ በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።
ኤርምያስ 12:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩና ሕዝቤን በበኣል እንዲምል እንዳስተማሩት ሁሉ፣ ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው በስሜ ቢምሉ፣ በዚያ ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በበዓል እንዲምል ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ‘በሕያው ጌታ እምላለሁ!’ ብለው እንዲምሉ የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩ፥ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሕዝቤን አካሄድ በሙሉ ልባቸው ተቀብለው እነርሱ ከዚህ በፊት ሕዝቤን በባዓል ስም መማል እንዳስተማሩአቸው ዐይነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የሚምሉ ከሆነ በሕዝቤ መካከል እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበዓል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ ፈጽመው ቢማሩ፥ በዚያ ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በበኣል ይምሉ ዘንድ ሕዝቤን እንዳስተማሩ በስሜ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! ብለው ይምሉ ዘንድ የሕዝቤን መንገድ በትጋት ቢማሩ፥ በዚያን ጊዜ በሕዝቤ መካከል ይመሠረታሉ። |
አንቺ ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ የተዋብሽ ሆይ፤ የማታውቂ ከሆነ፣ የበጎቹን ዱካ ተከተዪ፤ የፍየል ግልገሎችሽንም፣ በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።
ብዙ አሕዛብ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ እግዚአብሔር ተራራ፣ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ በጐዳናውም እንድንሄድ፤ መንገዱን ያስተምረናል።” ሕግ ከጽዮን፣ የእግዚአብሔርም ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።
እርሱም፣ “ባሪያዬ መሆንህ፣ የያዕቆብን ነገዶች እንደ ገና መመለስህ፣ የጠበቅኋቸውን እስራኤል መልሰህ ማምጣት ለአንተ ቀላል ነገር ነው፤ ድነቴን እስከ ምድር ዳርቻ እንድታመጣ፣ ለአሕዛብ ብርሃን አደርግሃለሁ” አለኝ።
ስለዚህ በምድሪቱ ላይ በረከትን የሚጠራ፣ በእውነት አምላክ ስም ይባረካል፤ በምድሪቱ መሐላን የሚምል፣ በእውነት አምላክ ስም ይምላል፤ ያለፉት ችግሮች ተረስተዋል፤ ከዐይኖቼም ተሰውረዋል።
ብርታቴና ምሽጌ፣ በመከራ ቀን መጠጊያዬ የሆንህ እግዚአብሔር ሆይ፤ አሕዛብ ከምድር ዳርቻ፣ ወደ አንተ መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “አባቶቻችን ለአንዳች ነገር ያልረቧቸውን ከንቱ ጣዖቶች፣ የሐሰት አማልክትን ወረሱ።
በዚያ ጊዜ ኢየሩሳሌምን፣ ‘የእግዚአብሔር ዙፋን’ ብለው ይጠሯታል፤ መንግሥታትም ሁሉ የእግዚአብሔርን ስም ለማክበር በኢየሩሳሌም ይሰበሰባሉ፤ የክፉ ልባቸውንም እልኸኝነት ከእንግዲህ አይከተሉም።
“ታዲያ፣ እንዴት ይቅር ልልሽ እችላለሁ? ልጆችሽ ትተውኛል፤ እውነተኛውን አምላክ ትተው አማልክት ባልሆኑት ምለዋል፤ እስኪጠግቡ ድረስ መገብኋቸው፤ እነርሱ ግን አመነዘሩ፤ ወደ ጋለሞቶችም ቤት ተንጋጉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “መንታ መንገድ ላይ ቁሙ፣ ተመልከቱም፤ መልካሟን፣ የጥንቷን መንገድ ጠይቁ፤ በርሷም ላይ ሂዱ። ለነፍሳችሁ ዕረፍት ታገኛላችሁ፤ እናንተ ግን፣ ‘በርሷ አንሄድም’ አላችሁ።
ለባሪያዎቼ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃልና ሥርዐት በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሰምን? “እነርሱም ንስሓ ገብተው እንዲህ አሉ፤ ‘የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር በወሰነው መሠረት፣ ለሥራችንና ለመንገዳችን የሚገባውን አድርጎብናል።’ ”
“በዚያ ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፤ የእኔም ሕዝብ ይሆናሉ። በመካከልሽ እኖራለሁ፤ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወደ አንቺ እንደ ላከኝም ታውቃላችሁ።
ከቅርንጫፎቹ አንዳንዶቹ ቢሰበሩ፣ አንተም የበረሓ ወይራ ሆነህ ሳለ በሌሎቹ መካከል ገብተህ ከተጣበቅህና ከወይራው ዘይት ሥር የሚገኘውን በረከት ተካፋይ ከሆንህ፣
እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤ “ ‘እኔ ሕያው ነኝና’ ይላል ጌታ፤ ‘ጕልበት ሁሉ ለእኔ ይንበረከካል፤ ምላስም ሁሉ ለእግዚአብሔር ይመሰክራል።’ ”
ከዚህ ዕደሪ፤ ሲነጋም ሰውየው ሊቤዥሽ ከፈለገ፣ መልካም ነው፤ ይቤዥሽ፤ የማይፈልግ ከሆነ ግን በሕያው እግዚአብሔር እምላለሁ፤ እኔ እቤዥሻለሁ፤ እስኪነጋም ድረስ እዚሁ ተኚ።”