ሴላም ደግሞ ቱባልቃይን የተባለ ወንድ ልጅ ነበራት፤ እርሱም ከብረትና ከናስ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እየቀረጸ የሚሠራ ነበር። የቱባልቃይን እኅት ናዕማ ትባል ነበር።
ዘፍጥረት 4:23 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላሜሕ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤ “ዓዳና ሴላ ሆይ ስሙኝ፤ የላሜሕ ሚስቶች ሆይ አድምጡኝ፤ አንድ ሰው ቢያቈስለኝ፣ ጕልማሳው ቢጐዳኝ፣ ገደልሁት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላሜሕም ለሚስቶቹ፥ “ዓዳ እና ጺላ፥ እስቲ አድምጡኝ፥ እናንት የላሜሕ ሚስቶች ሆይ፥ የምለውን ስሙኝ፤ ቢያቆስለኝ ጐልማሳውን ገደልኩ ብላቴናውንም ስለ መወጋቴ ገደልኩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላሜክ ሚስቶቹን እንዲህ አላቸው፤ እናንተ “ዓዳ እና ጺላ የላሜክ ሚስቶች ሆይ፥ እስቲ አድምጡኝ፥ የምለውን ስሙ፤ አንድ ወጣት መትቶ ስላቈሰለኝ ገደልኩት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው፥ “እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገሬንም አድምጡ፤ እኔ ጐልማሳውን ስለ መቍሰሌ፤ ብላቴናውንም ስለ መወጋቴ ገድየዋለሁና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላሜሕም ለሚስቶቹ ለዓዳና ለሴላ አላቸው፤ እናንት የላሜሕ ሚስቶች ቃሌን ስሙ፤ ነገሬን አድምጡ፤ |
ሴላም ደግሞ ቱባልቃይን የተባለ ወንድ ልጅ ነበራት፤ እርሱም ከብረትና ከናስ ልዩ ልዩ መሣሪያዎችን እየቀረጸ የሚሠራ ነበር። የቱባልቃይን እኅት ናዕማ ትባል ነበር።
“ ‘ወገንህን አትበቀል፤ ወይም በመካከልህ ከሚኖር በማንኛውም ሰው ላይ ቂም አትያዝ፤ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
በቀል የእኔ ነው፤ እኔ ብድራትን እመልሳለሁ፤ ጊዜው ሲደርስ እግራቸው ይሰናከላል፤ የመጥፊያቸው ቀን ቀርቧል፤ የሚመጣባቸውም ፍርድ ፈጥኖባቸዋል።”
ኢዮአታም ይህ በተነገረው ጊዜ፣ በገሪዛን ተራራ ጫፍ ላይ ወጥቶ ድምፁን ከፍ በማድረግ እንዲህ አላቸው፤ “የሴኬም ገዦች ሆይ፤ እግዚአብሔር ይሰማችሁ ዘንድ እኔን ስሙኝ።