ዘፍጥረት 30:13 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያም፣ “ምንኛ ደስተኛ ሆንሁ ከእንግዲህ ሴቶች ደስተኛዋ ይሉኛል” አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ አወጣችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፥ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፥ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያም “እጅግ ደስ ብሎኛል፤ ከእንግዲህ ወዲያ ሴቶች ሁሉ ‘ደስተኛዋ ሴት!’ ይሉኛል” ስትል ስሙን አሴር ብላ ጠራችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም፥ “እኔ ብፅዕት ነኝ፤ ሴቶች ያመሰግኑኛልና” አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም፦ ደስታ ሆነልኝ፤ ሴቶች ያመሰግኑኛልና አለች፤ ስሙንም አሴር ብላ ጠራችው። |
እንከን የሌለባት ርግቤ ግን ልዩ ናት፤ እርሷ ለወለደቻት የተመረጠች፣ ለእናቷም አንዲት ናት፤ ቈነጃጅት አይተው “የተባረክሽ ነሽ” አሏት፤ ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኗት።