ዘፍጥረት 10:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነዚህም በየነገዳቸው፣ በየጐሣቸውና በየቋንቋቸው ተከፋፍለው በባሕር ዳርና በደሴቶች፣ በየምድራቸው የሚኖሩ ሕዝቦች ወጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነዚህም በባሕር ዳርቻ ሕዝቦች፥ ሁሉም በየምድራቸው፥ በየቋንቋቸው፥ በየነገዳቸው፥ በየሕዝባቸው ተከፋፍለው የሚኖሩ የያፌት ልጆች ዘር ናቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነዚህ ሁሉ በባሕር ዳርቻና በደሴቶች ላይ ለሚኖሩ የያፌት ዘሮች ቅድመ አያቶች ናቸው፤ በየአገራቸውና በየጐሣቸውም ተከፋፍለው የሚኖሩ ሕዝቦች ነበሩ፤ እያንዳንዱም ጐሣ የሚነጋገርበት የራሱ ቋንቋ ነበረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው፥ በየቋንቋቸው፥ በየነገዳቸው፥ በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ። |
የኖኅ ወንዶች ልጆች ጐሣዎች እንደ ትውልዳቸው በየነገዳቸው እነዚህ ነበሩ። ከጥፋት ውሃ በኋላ ሕዝቦች በምድር ላይ የተሠራጩት ከእነዚሁ ነው።
በዚያ ቀን፣ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደ ገና የተረፈውን የሕዝቡን ቅሬታ ከአሦር፣ ከግብጽ፣ ከጳትሮስ፣ ከኢትዮጵያ፣ ከኤላም፣ ከባቢሎን፣ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።
እናንተ ወደ ባሕር የምትወርዱ፣ በዚያም ያላችሁ ሁሉ፣ ደሴቶችና በዚያ የምትኖሩ በሙሉ፣ ለእግዚአብሔር አዲስ መዝሙር፣ ከምድር ዳርቻም ምስጋናውን ዘምሩ።
እናንተ ደሴቶች ስሙኝ፤ እናንተ በሩቅ ያላችሁ ሕዝቦች ይህን አድምጡ፤ በእናቴ ማሕፀን ሳለሁ እግዚአብሔር ጠራኝ፤ ከመወለዴ በፊት በስም ጠራኝ።
ጽድቄ በፍጥነት እየቀረበ፣ ማዳኔም እየደረሰ ነው፤ ክንዴም ለመንግሥታት ፍትሕን ያመጣል፤ ደሴቶች ወደ እኔ ይመለከታሉ፤ ክንዴንም በተስፋ ይጠብቃሉ።
በርግጥ ደሴቶች እኔን ተስፋ ያደርጋሉ፤ እርሱ ክብሩን ስላጐናጸፈሽ፣ ለእስራኤል ቅዱስ፣ ለእግዚአብሔር አምላክሽ ክብር፣ ከሩቅ ወንዶች ልጆችሽን፣ ከነብራቸውና ከነወርቃቸው ለማምጣት፣ የተርሴስ መርከቦች ቀድመው ይወጣሉ።
“ጌታ እግዚአብሔር ጢሮስን እንዲህ ይላል፤ ‘የቈሰሉት ሲያቃስቱ፣ በውስጥሽም ጭፍጨፋ ሲካሄድ፣ ከውድቀትሽ ድምፅ የተነሣ ደሴቶች አይነዋወጡምን?
ከዚህም በኋላ በባሕር ጠረፍ ወዳሉት አገሮች ፊቱን በመመለስ ብዙዎቹን ይይዛል፤ ነገር ግን አንድ አዛዥ ትዕቢቱን ያከሽፍበታል፤ በራሱም ላይ ይመልስበታል።
እግዚአብሔር የምድሪቱን አማልክት ሁሉ በሚደመስስበት ጊዜ፣ በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በየባሕሩ ጠረፍ የሚኖሩ ሕዝቦች፣ እያንዳንዳቸው በያሉበት ሆነው ለርሱ ይሰግዳሉ።