ዘዳግም 4:20 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናንተን ግን ልክ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ርስቱ ትሆኑለት ዘንድ፣ አምላካችሁ እግዚአብሔር እናንተን ከብረት ማቅለጫ ምድጃ፣ ከግብጽ አውጥቶ አመጣችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንተን ግን ጌታ ወስዶ፥ እንደ ዛሬው ሁሉ የርስቱ ሕዝብ እንድትሆኑለት፥ ከብረት እቶን ከግብጽ አውጥቷችኋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን እሳት እንደሚነድበት የብረት ምድጃ ከሆነችው ከግብጽ መንጥቆ እግዚአብሔር ያወጣችሁ ዛሬ እንደ ሆናችሁት ሁሉ ለራሱ የተለያችሁ ወገኖቹ እንድትሆኑ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንተን ግን እንደ ዛሬው ሁሉ የርስቱ ሕዝብ ትሆኑለት ዘንድ እግዚአብሔር ወስዶ ከብረት እቶን ከግብፅ አወጣችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንተን ግን እንደ ዛሬው ሁሉ የርስቱ ሕዝብ ትሆኑለት ዘንድ እግዚአብሔር ወስዶ ከብረት እቶን ከግብፅ አወጣችሁ። |
ጭቃ በማስቦካት፣ ጡብ በማሠራትና በዕርሻም ሁሉ እያስጨነቁ ከባድ ሥራ እንዲሠሩ በማድረግ ሕይወታቸውን አስመረሩ፤ ግብጻውያኑ በሚያሠሯቸው ከባድ ሥራ ሁሉ ፈጽሞ አይራሩላቸውም ነበር።
“አቤቱ ጌታ ሆይ፤ በፊትህ ሞገስ አግኝቼ ከሆነ፣ ጌታ ከእኛ ጋራ ይሂድ፤ ይህ ዐንገተ ደንዳና ሕዝብ ቢሆንም እንኳ፣ ክፋታችንንና ኀጢአታችንን ይቅር በል፤ እንደ ርስትህም አድርገህ ውሰደን።”
በኔጌብ ስላሉት እንስሳት የተነገረ ንግር፤ መልእክተኞች ሀብታቸውን በአህያ፣ ውድ ዕቃዎቻቸውን በግመል ጭነው፣ ተባዕትና እንስት አንበሶች፣ መርዘኛና ተወርዋሪ እባቦች በሚኖሩበት፣ መከራና ጭንቅ ባለበት ምድር ዐልፈው፣ ወደማይጠቅማቸው ወደዚያ ሕዝብ፣
ይህም ትእዛዝ የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር፣ ከብረት ማቅለጫው ምድጃ ባወጣኋቸው ጊዜ ድምፄን ቢሰሙ፣ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቁ፣ እነርሱ ሕዝቤ፣ እኔም አምላካቸው እንድሆን የሰጠኋቸው ቃል ነው፤
ናቡከደነፆርም ወደሚነድደው የእቶን እሳት በር ቀረብ ብሎ ከፍ ባለ ድምፅ፣ “እናንተ የልዑል አምላክ አገልጋዮች ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብደናጎ፤ ኑ ውጡ! ወደዚህ ኑ!” አላቸው። ስለዚህ ሲድራቅ፣ ሚሳቅና አብድናጎ ከእሳቱ ወጡ፤
እንዲሁም በርሱ የተጠራችሁለት ተስፋ፣ ይህም በቅዱሳኑ ዘንድ ያለውን ክቡር የሆነውን የርስቱን ባለጠግነት ምን እንደ ሆነ ታውቁ ዘንድ የልባችሁ ዐይኖች እንዲበሩ
ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ ለራሱ የተለየ ሕዝብ እንድትሆንለት እግዚአብሔር በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ አንተን መርጦሃል።
አንተ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቅዱስ ሕዝብ ስለ ሆንህ፣ አምላክህ እግዚአብሔር የራሱ ሕዝብ፣ ርስትም እንድትሆንለት በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ መረጠህ።
እንዲህም በማለት ወደ እግዚአብሔር ጸለይሁ፤ “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ በታላቅ ኀይልህ የተቤዠኸውንና በኀያል ክንድህ ከግብጽ ያወጣኸውን፣ ያንተ ርስት የሆነውን ሕዝብህን አታጥፋ።
እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን የእግዚአብሔርን ታላቅ ሥራ እንድታውጁ የተመረጠ ትውልድ፣ የንጉሥ ካህናት፣ የተቀደሰ ሕዝብ፣ እግዚአብሔር ገንዘቡ ያደረገው ሕዝብ ናችሁ።