2 ሳሙኤል 23:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው፤ “በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፣ ልዑል ከፍ ከፍ ያደረገው ሰው፣ የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ፣ የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። ከፍ ከፍ የተደረገው፥ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፥ የእስራኤል ተወዳጁ ዘማሪ የሆነው፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት የትንቢት ቃል ይህ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፥ በእስራኤልም ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዳዊትም የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ የያዕቆብም አምላክ የቀባው፥ የታማኙ ሰው፥ በእስራኤል ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የታማኙ የእሴይ ልጅ የዳዊት ንግግር ይህ ነው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዳዊትም የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው። ከፍ ከፍ የተደረገው፥ በያዕቆብም አምላክ የተቀባው፥ በእስራኤል ዘንድ መልካም ባለ ቅኔ የሆነ፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት ንግግር፥ |
እርሱም፣ “ከእናንተ ጋራ በነበርሁበት ጊዜ፣ ‘በሙሴ ሕግ፣ በነቢያትና በመዝሙር መጻሕፍት ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ ይፈጸም ዘንድ ይገባል’ ብዬ የነገርኋችሁ ቃሌ ይህ ነው” አላቸው።
የክርስቶስ ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ እርስ በርሳችሁ በጥበብ ሁሉ ተማማሩ፤ ተመካከሩ፤ በመዝሙርና በማሕሌት፣ በመንፈሳዊም ቅኔ በማመስገን በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ።
ዳዊት በይሁዳ የቤተ ልሔሙ ሰው የኤፍራታዊው የእሴይ ልጅ ነበር። እሴይ ስምንት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ በሳኦልም ዘመን ያረጀና ዕድሜው የገፋ ሰው ነበር።
ከእግዚአብሔር ጋራ የሚጣሉ ይደቃሉ፤ እርሱ ከሰማይ ያንጐደጕድባቸዋል፤ እግዚአብሔር እስከ ምድር ዳርቻ ይፈርዳል። “ለንጉሡ ኀይልን ይሰጣል፤ የመሲሑንም ቀንድ ከፍ ከፍ ያደርጋል።”