2 ሳሙኤል 15:18 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹ ሁሉ፣ ከሊታውያን፣ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጋት ዐብረውት የመጡትን ስድስት መቶ ጋታውያንን ሁሉ ጨምሮ ተሰልፈው በንጉሡ ፊት ዐለፉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አገልጋዮቹ ሁሉ፥ ከሊታውያን፥ ፈሊታውያን እንዲሁም ከጌት አብረውት የመጡትን ስድስት መቶ ጌታውያን ሁሉን ጨምሮ ተሰልፈው በንጉሡ ፊት ዐለፉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ባለሟሎቹ ሁሉ በእርሱ በኩል አለፉ፤ የዳዊት ክብር ዘበኞች የነበሩት ከሪታውያንና ፈሊታውያን፥ እንዲሁም ከጋት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያን በንጉሡ ፊት አለፉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴኖቹም ሁሉ ተከተሉት፤ ኬልቲያውያንና ፌልታውያንም ሁሉ በምድረ በዳ በወይራ ሥር ቆሙ። ሕዝቡም ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሄዱ ነበር። ከእርሱ ጋር ያሉ ሰዎችም ሁሉ ስድስት መቶ ነበሩ። ከእርሱ ጋር ፌልታውያንና ኬልቲያውያን፥ በእግራቸው ከጌት የመጡ ስድስት መቶ ጌታውያንም ነበሩ። በንጉሡም ፊት ይሄዱ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎቹም ሁሉ በፊቱ አለፉ፥ ከሊታውያንና ፈሊታውያንም ሁሉ፥ ከእርሱም በኋላ ከጌት የመጡት ስድስት መቶው ጌታውያን ሁሉ በንጉሡ ፊት አለፉ። |
ዳዊትም ሰራዊቱን ሲሦውን በኢዮአብ፣ ሲሦውን በኢዮአብ ወንድም በጽሩያ ልጅ በአቢሳ፣ ሲሦውን ደግሞ በጋታዊው በኢታይ አዛዥነት ሥር ላካቸው። ንጉሡም ለሰራዊቱ፣ “እኔ ራሴም ዐብሬአችሁ በርግጥ እወጣለሁ” አላቸው።
ስለዚህ የኢዮአብ ሰዎች፣ ከሊታውያን፣ ፈሊታውያን እንዲሁም ሌሎች ኀያላን ጦረኞች በሙሉ በአቢሳ አዛዥነት ወጡ፤ ከኢየሩሳሌም የወጡትም የቢክሪ ልጅ ሳቤዔን ለማሳደድ ነበር።
ስለዚህ ዳዊት የእግዚአብሔር ታቦት ዐብሮት እንዲሆን ወደ ዳዊት ከተማ ይዞት ለመሄድ አልፈለገም፤ በዚህ ፈንታ አቅጣጫ ለውጦ የጋት ሰው ወደ ሆነው ወደ አቢዳራ ቤት ወሰደው።
ስለዚህ ካህኑ ሳዶቅ፣ ነቢዩ ናታን፣ የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ ከሊታውያንና ፈሊታውያን ወርደው ሰሎሞንን በንጉሥ ዳዊት በቅሎ አስቀምጠው በማጀብ ወደ ግዮን አመጡት።
ስለዚህ ዳዊትና ስድስት መቶ የሚሆኑ ሰዎቹ ከቅዒላ ተነሥተው መሄድ ወደሚችሉበት ቦታ ሁሉ ሄዱ፤ ዳዊት ከቅዒላ መሸሹን በሰማ ጊዜ፣ ሳኦል ወደዚያ መሄዱን ተወ።
ዳዊትም ሰዎቹን፣ “በሉ ሁላችሁም ሰይፋችሁን ታጠቁ” አላቸው። ስለዚህ ሁሉም ሰይፋቸውን ታጠቁ፤ ዳዊትም የራሱን ታጠቀ። አራት መቶ ያህል ሰዎች ከዳዊት ጋራ ሲወጡ መቶ ያህሉ ግን ጓዝ ለመጠበቅ ቀሩ።
ዳዊትና ሰዎቹ በጋት በአንኩስ ዘንድ ተቀመጡ፤ እያንዳንዱ ሰው ከቤተ ሰቡ ጋራ ነበረ፤ ዳዊትም ከሁለቱ ሚስቶቹ ጋራ፣ ከኢይዝራኤላዊቷ ከአኪናሆምና የናባል ሚስት ከነበረችው ከቀርሜሎሳዊቷ አቢግያ ጋራ ነበር።
በሦስተኛው ቀን ዳዊትና ሰዎቹ ጺቅላግ ደረሱ፤ በዚህ ጊዜ አማሌቃውያን ደቡቡን አገርና ጺቅላግን ወረው ነበር፤ ጺቅላግንም ወግተው አቃጥለው ነበር።