La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 18:36 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ነገር ግን ሕዝቡ ዝም አለ፤ ምንም መልስ አልሰጠም፤ ንጉሡ፣ “መልስ እንዳትሰጡ” ሲል አዝዞ ነበርና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሕዝቡም ቀደም ሲል ንጉሥ ሕዝቅያስ ባዘዛቸው መሠረት አንዲት ቃል ሳይናገሩ ዝም አሉ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ሕዝቡም ቀደም ሲል ንጉሥ ሕዝቅያስ ባዘዛቸው መሠረት አንዲት ቃል ሳይናገሩ ዝም አሉ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሕዝ​ቡም ዝም አሉ፥ አን​ዳ​ችም ቃል አል​መ​ለ​ሱ​ለ​ትም፤ ንጉሡ እን​ዳ​ይ​መ​ል​ሱ​ለት አዝዞ ነበ​ርና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሕዝቡም ዝም አሉ፤ አንዳችም አልመለሱለትም፤ ንጉሡ እንዳይመልሱለት አዝዞ ነበርና።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 18:36
9 Referencias Cruzadas  

ከእነዚህ አገሮች አማልክት ሁሉ አገሩን ከእጄ የታደገ ማን አለ? ታዲያ እግዚአብሔር ኢየሩሳሌምን እንዴት ከእጄ ሊታደጋት ይችላል?”


ከዚያም የቤተ መንግሥቱ አዛዥ የኬልቅያስ ልጅ ኤልያቄም፣ ጸሓፊው ሳምናስ እንዲሁም ታሪክ መዝጋቢው የአሳፍ ልጅ ዮአስ ልብሳቸውን ቀድደው ወደ ሕዝቅያስ መጡ፤ የጦር አዛዡ የተናገረውንም ሁሉ ነገሩት።


እኔ፣ “በአንደበቴ እንዳልበድል፣ መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ክፉዎችም በእኔ ዘንድ እስካሉ ድረስ፣ ልጓም በአፌ አስገባለሁ” አልሁ።


ሞኝን እንደ ቂልነቱ አትመልስለት፤ አለዚያ አንተም ራስህ እንደ እርሱ ትሆናለህ።


ፌዘኛን የሚገሥጽ ሁሉ ስድብን በራሱ ላይ ያመጣል፤ ክፉውን ሰው የሚዘልፍ ሁሉ ውርደት ያገኘዋል።


ለመቅደድ ጊዜ አለው፤ ለመስፋትም ጊዜ አለው፤ ለዝምታ ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፤


ስለዚህ አስተዋይ ሰው በእንዲህ ያለ ጊዜ ዝም ይላል፤ ቀኖቹ ክፉዎች ናቸውና።


“በእግሮቻቸው እንዳይረግጡት፣ ተመልሰውም ነክሰው እንዳይቦጫጭቋችሁ፣ የተቀደሰ ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቈቻችሁንም በዕሪያ ፊት አትጣሉ።