1 ሳሙኤል 2:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም “የኀያላን ቀስቶች ተሰባብረዋል፤ ደካሞች ግን በኀይል ታጥቀዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኀያላን ቀስቶች ተሰበሩ፤ ደካሞች ግን በብርታት ታጥቀዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኀያላን ቀስቶች ተሰበሩ፤ ደካሞች ግን ብርታትን አግኝተው ጠነከሩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኀያላንን ቀስት ሰብሮአል፤ ደካሞችንም ኀይልን አስታጥቋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኃያላንን ቀስት ሰብሮአል፥ ደካሞችም በኃይል ታጥቀዋል። |
ከእስረኞች ጋራ ከመርበትበት፣ ከታረዱትም ጋራ ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።
የሚዋጋችሁን የባቢሎናውያንን ሰራዊት ሁሉ አሸንፋችሁ፣ ቍስለኞች ብቻ በድንኳኖቻቸው ውስጥ ቢቀሩ እንኳ፤ እነዚህ ሰዎች መጥተው ይህችን ከተማ ያቃጥሏታል።”
በባቢሎን ላይ አጥፊ ይመጣል፤ ጦረኞቿ ይማረካሉ፤ ቀስታቸውም ይሰበራል፤ እግዚአብሔር ግፍን የሚበቀል፣ ተገቢውንም ሁሉ የሚከፍል አምላክ ነውና።
እርሱ ግን፣ “ጸጋዬ ይበቃሃል፤ ኀይሌ ፍጹም የሚሆነው በድካም ጊዜ ነውና” አለኝ። ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ያድር ዘንድ፣ ይበልጥ ደስ እያለኝ በድካሜ እመካለሁ።
እንግዲህ ከዚህ በላይ ምን ልበል? ስለ ጌዴዎን፣ ስለ ባርቅ፣ ስለ ሳምሶን፣ ስለ ዮፍታሔ፣ ስለ ዳዊት፣ ስለ ሳሙኤል፣ እንዲሁም ስለ ነቢያት እንዳልተርክ ጊዜ የለም።