ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።
1 ሳሙኤል 18:4 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከነጦር ልብሱ፣ በተጨማሪም ሰይፉን፣ ቀስቱንና መታጠቂያውን ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናታን የለበሰውን ካባ አውልቆ ከነጦር ልብሱ፥ በተጨማሪም ሰይፉን፥ ቀስቱንና መታጠቂያውን ሰጠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የለበሰውንም ካባ አውልቆ ለዳዊት ሰጠው፤ እንዲሁም የጦር ልብሱን፥ ሰይፉን፥ ቀስቱንና መታጠቂያውን ጭምር ሰጠው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮናታንም የለበሰውን ካባ አውልቆ እርሱንና ልብሱን፥ ሰይፉንም፥ ቀስቱንም፥ ዝናሩንም ለዳዊት ሸለመው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮናታንም የለበሰውን ካባ አውልቆ እርሱንና ልብሱን ሰይፉንም ቀስቱንም መታጠቂያውንም ለዳዊት ሸለመው። |
ፈርዖንም ባለማኅተሙን ቀለበት ከጣቱ አውልቆ በዮሴፍ ጣት ላይ አደረገው፤ እንዲሁም ከጥሩ የተልባ እግር የተሠራ ልብስ አለበሰው፤ በዐንገቱም የወርቅ ሐብል አጠለቀለት።
በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፤ ነፍሴ በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች፤ ሙሽራ ራሱን እንደሚያሳምር፣ ሙሽራዪቱም በዕንቈቿ እንደምታጌጥ፣ የድነትን ልብስ አልብሶኛል፤ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛል።
እነርሱም ወገባቸውን በቀበቶ የታጠቁና በራሳቸው ላይ ተንጠልጣይ ያለው ጥምጥም የጠመጠሙ ነበሩ፤ ሁሉም የከለዳውያን ተወላጆችና የባቢሎን ሠረገላ አዛዦች ይመስሉ ነበር።
“አባቱ ግን ባሮቹን እንዲህ አላቸው፤ ‘ፈጥናችሁ ከሁሉ ምርጥ የሆነውን ልብስ አምጡና አልብሱት፤ ለጣቱ ቀለበት፣ ለእግሩም ጫማ አድርጉለት፤
ሳኦል በሚልከው በማናቸውም ስፍራ፣ ዳዊት ተልእኮውን በሚገባ ይፈጽም ስለ ነበር፣ በሰራዊቱ ላይ ሾመው፤ ይህም ሕዝቡን በሙሉ፣ የሳኦልንም የጦር ሹማምት ደስ አሠኘ።