እግዚአብሔርም የልጁን ጩኸት ሰማ። የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ አላት፤ “አጋር ሆይ፤ ምን ሆነሻል? ልጅሽ ከተኛበት ሲያለቅስ እግዚአብሔር ሰምቶታል፤ ስለዚህ አትፍሪ።
1 ሳሙኤል 11:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ፣ ሳኦል በሬዎቹን እየነዳ ከዕርሻ ተመለሰ፤ እርሱም፣ “ሕዝቡ የሚያለቅሰው ምን ሆኖ ነው?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም የኢያቢስ ሰዎች ያሏቸውን ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ሳኦል በሬዎቹን እየነዳ ከእርሻ ተመለሰ፤ እርሱም፥ “ሕዝቡ የሚያለቅሰው ምን ሆኖ ነው?” ሲል ጠየቀ። እነርሱም የያቢሽ ሰዎች ያሏቸውን ነገሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል በዚህ ጊዜ ጥንድ በሬዎቹን ይዞ ከዋለበት እርሻ በመመለስ ላይ ነበር፤ እርሱም “ምንድን ነው ነገሩ? ሰው ሁሉ የሚያለቅሰው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ፤ እነርሱም ከያቤሽ የመጡ መልእክተኞች የሚሉትን ወሬ ነገሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም፥ ሳኦል ከእርሻው አርፍዶ መጣ፤ ሳኦልም፥ “ሕዝቡ የሚያለቅስ ምን ሆኖ ነው?” አለ። የኢያቢስንም ሰዎች ነገር ነገሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ ሳኦል በሬዎቹን ተከትሎ ከእርሻው መጣ፥ ሳኦልም፦ ሕዝቡ የሚያለቅስ ምን ሆኖ ነው? አለ። የኢያቢስንም ሰዎች ነገር ነገሩት። |
እግዚአብሔርም የልጁን ጩኸት ሰማ። የእግዚአብሔር መልአክ ከሰማይ አጋርን እንዲህ አላት፤ “አጋር ሆይ፤ ምን ሆነሻል? ልጅሽ ከተኛበት ሲያለቅስ እግዚአብሔር ሰምቶታል፤ ስለዚህ አትፍሪ።
ስለዚህ ኤልያስ ከዚያ ተነሥቶ ሲሄድ፣ የሣፋጥን ልጅ ኤልሳዕን ዐሥራ ሁለት ጥማድ በሬ አውጥቶ ራሱ በዐሥራ ሁለተኛው ጥማድ በሬ ሲያርስ አገኘው። ኤልያስም ወደ እርሱ መጥቶ መጐናጸፊያውን በላዩ ጣለበት።
ከበስተኋላቸው ሆነው ሲጮኹባቸውም፣ የዳን ሰዎች ወደ ኋላቸው ዞረው ሚካን፣ “ሰዎችህን ለውጊያ አሰባስበህ መምጣትህ ምን ሆንህና ነው?” አሉት።