1 ጴጥሮስ 3:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሣራም አብርሃምን “ጌታዬ” እያለች ትታዘዘው ነበር፤ እናንተም ምንም ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ የእርሷ ልጆች ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሣራም አብርሃምን “ጌታዬ” እያለች ትታዘዘው ነበር፤ እናንተም ምንም ሳያስፈራችሁ መልካም ብታደርጉ የእርሷ ልጆች ናችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የታዘዙትም ሣራ አብርሃምን “ጌታዬ!” እያለች ትታዘዝለት እንደ ነበረው ዐይነት ነው፤ እናንተም መልካም የሆነውን ነገር ብታደርጉና አንዳች የሚያስፈራ ነገር ባያስደነግጣችሁ የእርስዋ ልጆች ናችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፥ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም ሣራ ለአብርሃም፥ ጌታ ብላ እየጠራችው ታዘዘችለት፤ እናንተም ከሚያስደነግጥ ነገር አንዳች እንኳ ሳትፈሩ መልካም ብታደርጉ ልጆችዋ ናችሁ። |
“እኔን የዋሸሽኝ፤ ማንን ፈርተሽ፣ ማንንስ ሠግተሽ ነው? እኔን ያላስታወስሽው፣ ይህንም በልብሽ ያላኖርሽው፣ እኔን ያልፈራሽው፣ ዝም ስላልሁ አይደለምን?
ጴጥሮስና ዮሐንስ ግን መልሰው እንዲህ አሏቸው፤ “ከእግዚአብሔር ይልቅ ለእናንተ መታዘዝ በእግዚአብሔር ፊት ይገባ እንደ ሆነ እስኪ እናንተው ፍረዱ!