ዘኍል 8:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው አሮንም እንዲህ አደረገ፤ በመቅረዙ ፊት ለፊት እንዲበሩ በማድረግም መብራቶቹን አኖረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት መብራቶቹ በመቅረዙ ላይ ሆነው ፊት ለፊት እንዲያበሩ አስቀመጣቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ ጌታ ሙሴን እንዳዘዘው በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን ለኰሰ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን አበራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሮንም እንዲሁ አደረገ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ በመቅረዙ ፊት መብራቶቹን ለኰሰ። |