ዘኍል 23:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በለዓምም “በዚህ ቦታም ሰባት መሠዊያዎችን ሥራልኝ፤ ሰባት ኰርማዎችና ሰባት የበግ አውራዎችም አምጣልኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በለዓምም፣ “ሰባት መሠዊያዎች እዚህ ሥራልኝ፤ ሰባት ኰርማዎችና ሰባት አውራ በጎችም አዘጋጅልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በለዓምም ባላቅን፦ “በዚህ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፥ በዚህም ሰባት ወይፈን ሰባትም አውራ በግ አዘጋጅልኝ” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በለዓምም ባላቅን፥ “በዚህ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፤ በዚህም ሰባት ወይፈን፥ ሰባትም አውራ በግ አዘጋጅልኝ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በለዓምም ባላቅን፦ በዚህ ሰባት መሠዊያዎች ሥራልኝ፥ በዚህም ሰባት ወይፈን ሰባትም አውራ በግ አዘጋጅልኝ አለው። |