La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘኍል 15:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለ ስእለት ወይም ስለ አንድነት አንድ ወይፈን ለሚቃጠል ቊርባን ወይም መሥዋዕት በምታቀርብበት ጊዜ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ ‘አንዱን ወይፈን ለተለየ ስእለት ወይም ለኅብረት የሚቀርብ የሚቃጠል መሥዋዕት ወይም የዕርድ መሥዋዕት አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር በምታዘጋጁበት ጊዜ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ለሚቃጠልም መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት ወይም ስእለትን ለመፈጸም ወይም ለአንድነት መሥዋዕት ወይፈንን ለጌታ ብታዘጋጅ፥

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለሚ​ቃ​ጠ​ልም መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ለሌላ መሥ​ዋ​ዕት፥ ወይም ስእ​ለ​ትን ለመ​ፈ​ጸም፥ ወይም ለደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ከላም ወገን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ብታ​ዘ​ጋጅ፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ለሚቃጠልም መሥዋዕት ወይም ለሌላ መሥዋዕት ወይም ስእለትን ለመፈጸም ወይም ለደኅንነት መሥዋዕት ወይፈንን ለእግዚአብሔር ብታዘጋጅ፥

Ver Capítulo



ዘኍል 15:8
10 Referencias Cruzadas  

ይኸውም ከቀንድ ከብቱ መካከል አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ቢፈልግ ምንም ነውር የሌለበትን ኰርማ መርጦ ያምጣ፤ እርሱም በእግዚአብሔር ፊት የሰመረ መሥዋዕት ይሆንለት ዘንድ በመገናኛው ድንኳን መግቢያ በር በኩል ያቅርበው።


ያም ሰው የእንስሳውን ሆድ ዕቃና የኋላ እግሮቹን በውሃ ይጠብ፤ ካህኑም መሥዋዕቱን በሙሉ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ይህም የሚቃጠል መሥዋዕት ነው። የዚህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል።


ማንም ሰው ስእለት ተፈጽሞለት ወይም የበጎ ፈቃድ ስጦታ አድርጎ የአንድነት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ቢያቀርብ፥ ተቀባይነት ማግኘት እንዲችል፥ እንስሳው ምንም ነውር የሌለበት ይሁን።


ማንኛውም ሰው ከቀንድ ከብቱ ለእግዚአብሔር የአንድነት መሥዋዕት በሚያቀርብበት ጊዜ ነውር የሌለበትን አንድ ኰርማ ወይም ላም መርጦ ያምጣ።


ይህ የሚቃጠል መሥዋዕት በመሆኑ የአሮን ልጆች በሚቃጠለው መሥዋዕት መሠዊያ ላይ ያቃጥሉት፤ ይህ ዐይነቱ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነው።


እንዲህ ዐይነቱ ስሕተት የተፈጸመው በማኅበሩ አለማወቅ ከሆነ አንድ ወይፈን አምጥተው መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡት፤ ከእርሱም ጋር ተገቢውን የእህልና የወይን ጠጅ ቊርባን ያቅርቡ፤ በተጨማሪም አንድ ተባዕት ፍየል ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት አድርገው ያቅርቡ።


ለመጠጥ ቊርባን የሊትር አንድ ሦስተኛ የወይን ጠጅ ታቀርባለህ፤ ይህም ሁሉ መሥዋዕት መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ይሆናል፤


ከወይፈኑ ጋር ሦስት ኪሎ በግማሽ ሊትር ዘይት የተለወሰ ምርጥ ዱቄት የእህል ቊርባን አቅርብ።


ቀጥሎም አንድ ወይፈንና ለእህል ቊርባን የተመደበውን በዘይት የተለወሰ ዱቄት ይውሰዱ፤ አንተም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት የሚቀርብ አንድ ወይፈን ውሰድ፤