እርሱ ግን በየጊዜው ብቻውን ወደ በረሓ እየሄደ ይጸልይ ነበር።
ኢየሱስ ግን ብዙ ጊዜ ወደ ገለልተኛ ስፍራ ወጥቶ ይጸልይ ነበር።
እርሱ ግን ገለል ብሎ ወደ በምድረ በዳዎች እየሄደ ይጸልይ ነበር።
እርሱ ግን ወደ ምድረ በዳ እየወጣ ይጸልይ ነበር።
ነገር ግን እርሱ ወደ ምድረ በዳ ፈቀቅ ብሎ ይጸልይ ነበር።
ሕዝቡንም ካሰናበተ በኋላ ለመጸለይ ብቻውን ወደ አንድ ተራራ ላይ ወጣ፤ በመሸም ጊዜ ኢየሱስ እዚያ ብቻውን ነበር።
ከዚህ በኋላ ከእነርሱ ተለይቶ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ።
ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስም ተጠመቀ፤ እርሱ ሲጸልይ ሳለ ሰማይ ተከፈተ፤
አንድ ቀን ኢየሱስ ለመጸለይ ወደ ተራራ ወጣ፤ እዚያ ሌሊቱን ሙሉ ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ዐደረ።
ኢየሱስ ይህን ከተናገረ ከስምንት ቀን በኋላ ጴጥሮስን፥ ዮሐንስንና ያዕቆብን አስከትሎ ለመጸለይ ወደ አንድ ተራራ ላይ ወጣ።
በሚጸልይበትም ጊዜ መልኩ ተለወጠ፤ ልብሱም ነጭ ሆኖ አንጸባረቀ፤
ሰዎቹ ግን በግድ ወስደው ሊያነግሡት እንዳሰቡ ባወቀ ጊዜ ኢየሱስ ብቻውን እንደገና ራቅ ብሎ ወደ ኮረብታ ሄደ።