ዕንባቆም 3:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመዝሙር የቀረበ የነቢዩ ዕንባቆም ጸሎት ይህ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዝማሬ የቀረበ የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት፤ በሺግዮኖት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት በሺግዮኖት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት በመዝሙር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የነቢዩ የዕንባቆም ጸሎት በመዝሙር። |
እግዚአብሔር ሆይ! ስላደረግኸው አስደናቂ ሥራ ሁሉ ሰምቼ እጅግ ፈራሁ፤ አሁንም በዘመናችን የቀድሞውን ሥራህን ደግመህ አድርግ፤ በየዘመናቱም እንዲታወቅ አድርግ፤ በምትቈጣበት ጊዜ እንኳ ምሕረትህን አታርቅ።