እግዚአብሔርም “ብዙ፤ ተባዙ፤ ዘራችሁ ምድርን ይሙላ፤ ምድርም በቊጥጥራችሁ ሥር ትሁን፤ በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሣዎች፥ በሰማይ በሚበርሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራችሁ” ብሎ ባረካቸው።
ዘፍጥረት 6:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሕይወት እንዲኖሩ ከየዐይነቱ ወፎች፥ ከየዐይነቱ እንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ከልዩ ልዩ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶች በየዐይነቱ ሁለት ሁለት ወደ አንተ ይምጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእያንዳንዱ የወፍ ወገን፣ ከእያንዳንዱ የእንስሳ ወገን፣ በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረታት ሁሉ በየወገናቸው በሕይወት ይቈዩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይመጣሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከወፍ እንደ ወገኑ፥ ከእንስሳም እንደ ወገኑ፥ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንደ ወገኑ በሕይወት ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆኑ ወደ አንተ ይግቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከወፎች ሁሉ በየወገናቸው፥ ከእንስሳም ሁሉ በየወገናቸው፥ በምድር ላይ ከሚሳቡ ተንቀሳቃሾች ሁሉ በየወገናቸው ከአንተ ጋር ይመገቡ ዘንድ ከሁሉም ሁለት ሁለት ወንድና ሴት እየሆኑ ወደ አንተ ይግቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከወፍ እንደ ወገኑ ከእንስሳም እንደ ወገኑ ከምድር ተንቀሳቃሽም ሁሉ እንድ ወገኑ በሕይውር ይኖሩ ዘንድ ሁለት ሁለት እየሆን ወደ አንተ ይግቡ። |
እግዚአብሔርም “ብዙ፤ ተባዙ፤ ዘራችሁ ምድርን ይሙላ፤ ምድርም በቊጥጥራችሁ ሥር ትሁን፤ በባሕር ውስጥ በሚኖሩ ዓሣዎች፥ በሰማይ በሚበርሩ ወፎችና በምድር ላይ በሚንቀሳቀሱ ሕያዋን ፍጥረቶች ሁሉ ላይ ሥልጣን ይኑራችሁ” ብሎ ባረካቸው።
እግዚአብሔር አምላክ ከምድር ዐፈር ወስዶ እንስሶችንና ወፎችን ሁሉ ፈጠረ፤ ምን ዐይነት ስም እንደሚያወጣላቸው ለማየት ወደ አዳም አመጣቸው፤ አዳም ለእያንዳንዱ ሕያው ፍጡር ያወጣለት ስም መጠሪያው ሆነ።
ከያንዳንዱ ዐይነት ወፍ ወንድና ሴት ሰባት ወንድ ሰባት ሴት አስገባ፤ ይህንንም የምታደርገው እያንዳንዱ ዐይነት እንስሳና ወፍ በሕይወት እንዲኖርና በምድር ላይ ለዘር እንዲተርፍ ነው።