ዘፍጥረት 6:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፥ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ወደ መርከቡ ግቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከአንተ ጋራ ግን ቃል ኪዳን እመሠርታለሁ። አንተና ወንዶች ልጆችህ፣ ሚስትህና የልጆችህ ሚስቶች ከአንተ ጋራ ወደ መርከቧ ትገባላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፥ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ይዘህ ወደ መርከቡ ትገባለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃል ኪዳኔንም ከአንተ ጋር አጸናለሁ፤ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን፥ የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃል ኪዳኔም ከአንተ ጋር አቆማለሁ ወደ መርከብም አንተ ልጆችህንና ሚስትህን የልጆችህንም ሚስቶች ይዘህ ትገባለህ። |
“በአንተና በዘርህ፥ በመጪውም ትውልድ መካከል ቃል ኪዳኔን ለዘለዓለም አጸናለሁ፤ በዚህም ዐይነት ለአንተና ከአንተ በኋላ ለሚመጣው ዘርህ አምላክ እሆናለሁ።
እግዚአብሔር ኖኅን እንዲህ አለው፤ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ብቻ ሆነህ ስላገኘሁህ፥ ከመላው ቤተሰብህ ጋር ወደ መርከቡ ግባ።
ገና በዐይን ስለማይታዩት ነገሮች እግዚአብሔር ባስጠነቀቀው ጊዜ ኖኅ እግዚአብሔርን በመፍራት ቤተሰቡን ለማዳን መርከብን የሠራው በእምነት ነው፤ በኖኅም እምነት ዓለም ኃጢአተኛ መሆኑ ታውቆ ተፈረደበት፤ ኖኅም በእምነት የሚገኘውን ጽድቅ ወረሰ።
እነዚህ በወህኒ ቤት የነበሩ መናፍስት ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲዘጋጅ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው ሳለ አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በዚያ መርከብ ውስጥ ገብተው በውሃ አማካይነት የዳኑት ቊጥራቸው ስምንት የሆነ ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው።
እንዲሁም የጽድቅ ሰባኪ የነበረውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ እግዚአብሔርን የማያመልኩ ሰዎች በነበሩበት ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ሲያመጣ ራርቶ የቀድሞውን ዓለም አልማረውም፤