በዚያን ምሽት ያዕቆብ ከዱር ሲመለስ፥ ልያ ከቤት ወደ እርሱ ወጥታ “በልጄ እንኮይ ስለ ገዛሁህ ዛሬ ሌሊት የምታድረው ከእኔ ጋር ነው” አለችው፤ ስለዚህ በዚያን ሌሊት ከእርስዋ ጋር ዐደረ።
ዘፍጥረት 30:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር የልያን ጸሎት ሰማ፤ ስለዚህ ፀነሰችና ለያዕቆብ አምስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደችለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር የልያን ጸሎት ሰማ፤ ፀነሰች፤ ለያዕቆብም ዐምስተኛውን ወንድ ልጅ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፥ ፀነሰችም፥ አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ሌሊት ከእርስዋ ጋር አደረ። እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፤ ፀነሰችም፤ አምስተኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም የልያን ጸሎት ሰማ፥ ፀነሰችም፥ አምስትኛ ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደች። |
በዚያን ምሽት ያዕቆብ ከዱር ሲመለስ፥ ልያ ከቤት ወደ እርሱ ወጥታ “በልጄ እንኮይ ስለ ገዛሁህ ዛሬ ሌሊት የምታድረው ከእኔ ጋር ነው” አለችው፤ ስለዚህ በዚያን ሌሊት ከእርስዋ ጋር ዐደረ።
ከዚያም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጭንቀት አይቻለሁ፤ በአስጨናቂዎቻቸው ምክንያት የሚጮኹትን ጩኸት ሰምቼአለሁ፤ ጭንቀታቸውንም ዐውቃለሁ።
መልአኩ ግን እንዲህ አለው፦ “ዘካርያስ ሆይ! አትፍራ! ጸሎትህ ተሰምቶልሃል፤ ሚስትህ ኤልሳቤጥ ወንድ ልጅ ትወልድልሃለች፤ ስሙንም ዮሐንስ ብለህ ትጠራዋለህ።