ዘፍጥረት 18:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሰዎቹ ለመሄድ ተነሡ፤ ሰዶምን ቊልቊል ወደሚያዩበት ስፍራም ደረሱ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎቹም ለመሄድ ሲነሡ፣ ቍልቍል ወደ ሰዶም ተመለከቱ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው ዐብሯቸው ወጣ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰዎቹም ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ፥ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚያም ሰዎች ከዚያ ተነሥተው ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ አቀኑ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ፤ አብርሃምም ተመልሶ በእግዚአብሔር ፊት ቆመ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሰዎቹም ከዚያ ተንሥተው ወደ ሰዶም አቀኑ፤ አብርሃምም ሊሸኛቸው አብሮአቸው ሄደ። |
ቀና ብሎም ሲመለከት ሦስት ሰዎች እዚያ ቆመው አየ፤ እንዳያቸውም ወዲያውኑ ሊያነጋግራቸው ወደ እነርሱ ሮጠ፤ ግንባሩም መሬት እስኪነካ ዝቅ ብሎ በመስገድ እጅ ነሣ፤
በዚያኑ ምሽት ሁለቱ መላእክት ወደ ሰዶም መጡ፤ በዚያን ጊዜ ሎጥ በከተማይቱ በር ተቀምጦ ነበር፤ መላእክቱን ባያቸው ጊዜ ሊያነጋግራቸው ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሄደ፤ ጐንበስ ብሎም እጅ ነሣቸውና፥
ስለዚህ እነርሱ በቤተ ክርስቲያን ተልከው ሄዱ፤ በፊንቄና በሰማርያ ሲያልፉም የአሕዛብን ወደ እግዚአብሔር መመለስ ተናገሩ፤ ይህም ዜና ክርስቲያኖችን ሁሉ አስደሰተ።
እዚያ የምንቈይበት ጊዜ ሲያልቅ ተለይተናቸው ጒዞአችንን ቀጠልን፤ ሁሉም ከሚስቶቻቸውና ከልጆቻቸው ጋር ሆነው እስከ ከተማው ውጪ ድረስ ሸኙን፤ በባሕሩም ዳር ተንበርክከን ከጸለይን በኋላ ተሰነባበትን።
ወደ እስፔን በምሄድበት ጊዜ እግረ መንገዴን ልጐበኛችሁ ዐቅጃለሁ። ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ደስ ብሎኝ ከቈየሁ በኋላ ጒዞዬን ለመቀጠል የሚያስችለኝን ርዳታ እንደምታደርጉልኝ ተስፋ አደርጋለሁ።
እነርሱም ስለ አደረግህላቸው የፍቅር ሥራ በማኅበረ ምእመናን ፊት መስክረዋል፤ አሁንም እግዚአብሔርን ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ በጒዞአቸው ብትረዳቸው መልካም ነው።