ገላትያ 4:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለተለዩ ቀኖችና ወሮች ለተወሰኑ የዓመት ክፍሎችና ዓመቶች ጥንቃቄ በማድረግ ልዩ ክብር ትሰጣላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልዩ የሆኑ ቀኖችን፣ ወሮችን፣ ወቅቶችንና ዓመታትን ታከብራላችሁ! መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቀኖችን፥ ወሮችን፥ ዘመናትንና ዓመታትን በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዕለትንና ወርን፥ ጊዜንና ዓመታትን ትጠብቃላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ። |
እንዲሁም አንዱ ቀን ከሌላው ቀን ይበልጥ ክቡር ነው ብሎ የሚያስብ ይኖር ይሆናል፤ ሌላው ደግሞ ቀኖች ሁሉ እኩል ክብር አላቸው እንጂ በቀኖች መካከል ልዩነት የለም ብሎ ያስባል። እንግዲህ ይህን በመሳሰለው ነገር እያንዳንዱ ሰው ከልቡ ያመነበትን ያድርግ።