በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ታላላቅ የባሕር አውሬዎችን፥ ሌሎችንም በውሃ ውስጥ የሚኖሩና የሚንቀሳቀሱ ልዩ ልዩ ፍጥረቶችን እንደየዐይነታቸው፥ እንዲሁም ልዩ ልዩ ወፎችን እንደየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።
ዘዳግም 4:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወይም በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን፥ ከምድር በታች በውሃ ውስጥ የሚኖሩትን የዓሣ ሁሉ ምስል አታድርጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይም በደረቱ የሚሳብ የማናቸውንም ፍጡር ወይም በውሃ ውስጥ የሚኖር የማናቸውንም ዓሣ ምስል እንዳታደርጉ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድርም ላይ በደረታቸው እየተሳቡ የሚንቀሳቀሱትን፥ ከምድር በታች በውሃ ውስጥ የሚኖሩትን የዓሣ ሁሉ ምስል አታድርጉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድርም ላይ የሚሽከረከረውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ አታድርጉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድርም ላይ የሚሽከረከረውን ሁሉ ምሳሌ፥ ከምድርም በታች በውኃ ውስጥ የሚኖረውን የዓሣን ሁሉ ምሳሌ እንዳታደርጉ፥ |
በዚህ ዐይነት እግዚአብሔር ታላላቅ የባሕር አውሬዎችን፥ ሌሎችንም በውሃ ውስጥ የሚኖሩና የሚንቀሳቀሱ ልዩ ልዩ ፍጥረቶችን እንደየዐይነታቸው፥ እንዲሁም ልዩ ልዩ ወፎችን እንደየዐይነታቸው ፈጠረ። እግዚአብሔርም ይህ መልካም መሆኑን አየ።
በሰማይ ላይ የምታዩአቸውን ፀሐይንና ጨረቃን ወይም ከዋክብትን ወይም የሰማይን ሠራዊት ሁሉ በማምለክና ለእነርሱ በመስገድ እንዳትፈተኑ ተጠንቀቁ፤ እግዚአብሔር አምላካችሁ እነዚህን ሁሉ ሌሎች ሕዝቦች ብቻ ያመልኩአቸው ዘንድ አሳልፎ ሰጥቶአቸዋል።