ዳንኤል 6:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጒድጓዱም አፍ ላይ ድንጋይ ተገጠመበት፤ ማንም ሰው ዳንኤልን አውጥቶ ለማዳን እንዳይሞክር ንጉሡ የራሱን መንግሥታዊ ማኅተምና የባለሟሎቹን ማኅተም አተመበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ድንጋይ አምጥተው በጕድጓዱ አፍ ላይ ገጠሙበት፤ ንጉሡም፣ በዳንኤል ላይ የተፈጸመው እንዳይለወጥ በራሱ የቀለበት ማኅተምና በመሳፍንቱ ቀለበቶች ዐተመበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድንጋይም አምጥተው በጕድጓዱ አፍ ላይ ገጠሙበት፥ ንጉሡም በዳንኤል ላይ የተደረገው እንዳይለወጥ በቀለበቱና በመኳንንቱ ቀለበት አተመው። |
ጴጥሮስን ካስያዘ በኋላ ወደ ወህኒ ቤት አስገባው፤ ከአይሁድ የፋሲካ በዓል በኋላ ለሕዝቡ እስኪያቀርበው ድረስ አራት አራት ሆነው እንዲጠብቁት ለአራት ጭፍሮች አስረከበው።
ሺህ ዓመት እስኪፈጸም ድረስ ሕዝቦችን እንዳያስት መልአኩ ዘንዶውን ወደ ጥልቁ ጒድጓድ ጣለው፤ ዘግቶም በማኅተም አሸገው፤ ከዚያ በኋላ ለጥቂት ጊዜ መፈታት ይገባዋል።