ዳንኤል 3:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሦስቱንም ሰዎች አስረው ወደሚነደው የእሳት ነበልባል ጒድጓድ ውስጥ ይጥሉአቸው ዘንድ ከሠራዊቱ መካከል ብርቱ የሆኑትን አዘዘ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከሰራዊቱም ብርቱ የሆኑትን ጥቂት ወታደሮች፣ ሲድራቅን፣ ሚሳቅንና አብደናጎን አስረው ወደሚንበለበለው የእቶን እሳት ውስጥ እንዲጥሏቸው አዘዘ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብድናጎንም ያስሩ ዘንድ፥ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ። |
እንግዲህ የመለከት፥ የእንቢልታ፥ የመሰንቆ፥ የክራር፥ የበገና፥ የዋሽንትና፥ የሙዚቃም ሁሉ ድምፅ ስትሰሙ ላቆምኩት ምስል በመሬት ላይ ተደፍታችሁ ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በሚነደው የእሳት ነበልባል ጒድጓድ ውስጥ ወዲያውኑ ትጣላላችሁ፤ ከእጄም የሚያድናችሁ አምላክ እንደሌለ ዕወቁ።”
በዚያን ጊዜ ናቡከደነፆር በሲድራቅ፥ በሚሳቅና በአብደናጎ ላይ እጅግ ተቈጥቶ መልኩ ተለዋወጠ፤ ስለዚህ እሳቱ ከቀድሞው ይበልጥ በሰባት እጥፍ ከፍ ብሎ እንዲነድ ትእዛዝ ሰጠ።
ስለዚህ ቀሚሳቸው፥ ሱሪያቸውና መጠምጠሚያቸው ሳይቀር ሙሉ ልብሳቸውን እንደ ለበሱ አስረው ወደሚነደው ወደ የእሳት ነበልባል ጒድጓድ ውስጥ ጣሉአቸው።