ኦርዮም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች በድንኳን ሰፍረው በጦር ሜዳ ይገኛሉ፤ የቃል ኪዳኑም ታቦት ከእነርሱ ጋር ነው፤ የጦር አለቃዬ ኢዮአብና የእርሱም የጦር መኰንኖች በሜዳ ሰፍረዋል፤ ታዲያ እኔ ወደ ቤቴ ሄጄ መብላት፥ መጠጣት፥ ከሚስቴም ጋር መተኛት እንዴት ይቻለኛል? ይህን የመሰለ ነገር ከቶ እንደማላደርግ በአንተ ሕይወት እምላለሁ!”
2 ሳሙኤል 11:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኦርዮ ወደ ቤቱ አለመሄዱን ዳዊት በሰማ ጊዜ “ብዙ ጊዜ ከቤተሰብህ ተለይተህ እነሆ አሁን ገና መመለስህ ነው፤ ታዲያ ወደ ቤትህ ያልሄድከው ስለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት፣ “ኦርዮን ወደ ቤቱ አልሄደም” መባሉን ሲሰማ ኦርዮን፣ “ከመንገድ ገና አሁን መግባትህ አይደለምን? ወደ ቤትህ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዳዊት፥ “ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” መባሉን ሲሰማ ኦርዮንን፥ “ከመንገድ ገና አሁን መግባትህ አይደለምን? ወደ ቤትህ ያልሄድኸው ለምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም” ብለው ለዳዊት ነገሩት፤ ዳዊትም ኦርዮን፥ “አንተ ከመንገድ የመጣህ አይደለህምን? ስለምን ወደ ቤትህ አልወረድህም?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኦርዮ ወደ ቤቱ አልሄደም ብለው ለዳዊት ነገሩት፥ ዳዊትም ኦርዮን፦ አንተ ከመንገድ የመጣህ አይደለምን? ስለ ምን ወደ ቤትህ አልወረድህም? አለው። |
ኦርዮም እንዲህ ሲል መልስ ሰጠ፤ “የእስራኤልና የይሁዳ ሰዎች በድንኳን ሰፍረው በጦር ሜዳ ይገኛሉ፤ የቃል ኪዳኑም ታቦት ከእነርሱ ጋር ነው፤ የጦር አለቃዬ ኢዮአብና የእርሱም የጦር መኰንኖች በሜዳ ሰፍረዋል፤ ታዲያ እኔ ወደ ቤቴ ሄጄ መብላት፥ መጠጣት፥ ከሚስቴም ጋር መተኛት እንዴት ይቻለኛል? ይህን የመሰለ ነገር ከቶ እንደማላደርግ በአንተ ሕይወት እምላለሁ!”
እግዚአብሔር ነቢዩን ናታንን ወደ ዳዊት ላከው፤ ናታንም ወደ ዳዊት ሄዶ እንዲህ አለው፤ “በአንድ ከተማ የሚኖሩ ሁለት ሰዎች ነበሩ፤ ከእነርሱ አንዱ ሀብታም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ድኻ ነበር፤