አባቱ ለእግዚአብሔር የተለዩ እንዲሆኑ ያደረጋቸውንና እርሱም ራሱ ከወርቅና ከብር አሠርቶ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ብቻ እንዲውሉ ያደረጋቸውን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ በቤተ መቅደስ አኖረ።
2 ነገሥት 18:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቅያስም በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ዕቃ ግምጃ ቤት የነበረውን ብር ሁሉ ሰብስቦ ላከለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ሕዝቅያስ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤቶች የሚገኘውን ብር ሁሉ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሕዝቅያስም በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ዕቃ ግምጃ ቤት የነበረውን ብር ሁሉ ሰብስቦ ላከለት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሡ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ብር ሁሉ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤትና በንጉሡ ቤተ መዛግብት የተገኘውን ብር ሁሉ ሰጠው። |
አባቱ ለእግዚአብሔር የተለዩ እንዲሆኑ ያደረጋቸውንና እርሱም ራሱ ከወርቅና ከብር አሠርቶ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ብቻ እንዲውሉ ያደረጋቸውን ንዋያተ ቅድሳት ሁሉ በቤተ መቅደስ አኖረ።
የይሁዳ ንጉሥ ኢዮአስም ከእርሱ በፊት የነበሩትን ነገሥታት፥ ማለትም ኢዮሣፍጥ፥ ኢዮራምና አካዝያስ ለእግዚአብሔር ለይተው ያኖሩትን መባና የራሱን መባ ጨምሮ በቤተ መቅደስና በቤተ መንግሥት ግምጃ ቤቶች የነበረውን ወርቅ ሁሉ በመሰብሰብ ገጸ በረከት አድርጎ ለንጉሥ አዛሄል ላከለት፤ ሐዛኤልም ይህን ተቀብሎ ሠራዊቱን ከኢየሩሳሌም መለሰ።
እንዲሁም በቤተ መቅደሱ መግቢያ በሮች ላይ ተለብጦ የነበረውን ወርቅና እርሱም ራሱ በቤተ መቅደሱ የበር ዐምዶች ላይ ለብጦት የነበረውን ወርቅ ጭምር ወደ ሰናክሬም ላከ።
ስለዚህም አሳ ከቤተ መቅደስና ከቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤት ብርና ወርቅ በማውጣት በደማስቆ ይኖር ለነበረው ለሶርያው ንጉሥ ቤንሀዳድ ስጦታ አድርጎ ላከለት፤ ከስጦታውም ጋር እንዲህ የሚል መልእክት ነበረ፤
ሕዝቅያስም መልእክተኞቹን በደስታ ተቀበላቸው፤ በቤተ መንግሥቱም የዕቃ ግምጃ ቤት ያለውን ሀብት በሙሉ ብሩንና ወርቁን፥ ቅመማ ቅመሙንና፥ ሽቶውን፥ የጦር መሣሪያውንና በዕቃ ቤት ያለውን ንብረት ሁሉ አሳያቸው፤ በቤተ መንግሥቱ ግምጃ ቤትም ሆነ በመንግሥቱ በማንኛውም ስፍራ ካለው ሀብት ሁሉ ሕዝቅያስ ያላሳያቸው ምንም ነገር አልነበረም።