La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 12:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ካህናቱም በዚህ ተስማምተው ቤተ መቅደሱን ለማደስ የነበራቸውን ተግባር አቆሙ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ካህናቱም ከእንግዲህ ከሕዝቡ ገንዘብ ላለመሰብሰብና ቤተ መቅደሱንም ራሳቸው ላለማደስ ተስማሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ካህናቱም በዚህ ተስማምተው ቤተ መቅደሱን ለማደስ የነበራቸውን ተግባር አቆሙ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ካህ​ና​ቱም “ከሕ​ዝቡ ገን​ዘ​ቡን አን​ወ​ስ​ድም፤ በቤ​ቱም ውስጥ የተ​ና​ዱ​ትን አን​ጠ​ግ​ንም፥” ብለው ተስ​ማሙ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኢዮአስም ካህኑን ዮዳሄንና ካህናቱን ጠርቶ “በመቅደሱ ውስጥ የተናዱትን ስፍራዎች ስለ ምን አትጠግኑአቸውም? ከእንግዲህ ወዲያ ገንዘቡ ለቤቱ መጠገኛ ይሰጥ እንጂ ከሚያመጡት ሰዎች አትቀበሉ፤” አላቸው።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 12:8
4 Referencias Cruzadas  

ስለዚህም ኢዮአስ ዮዳሄንና ሌሎቹንም ካህናት ወደ እርሱ ጠርቶ “ቤተ መቅደሱን ያላደሳችሁበት ምክንያት ምንድን ነው? ከዛሬ ጀምሮ የምትቀበሉትን ገንዘብ መያዝ የለባችሁም፤ ለቤተ መቅደሱ እድሳት ይውል ዘንድ ገንዘቡን አስረክቡ” አላቸው።


ከዚህ በኋላ ዮዳሄ አንድ ሣጥን ወስዶ በመክደኛው ላይ ቀዳዳ አበጀ፤ ሣጥኑንም ወስዶ ወደ ቤተ መቅደስ ሲገቡ በስተ ቀኝ በሚገኘው መሠዊያ አጠገብ አኖረው፤ የየዕለቱ ተረኞች የነበሩትም ካህናት ለስግደት የሚመጡት ሰዎች የሚሰጡትን የገንዘብ መባ እየተቀበሉ በሣጥኑ ውስጥ ያስገቡት ነበር፤


“ሒልቂያ ተብሎ ወደሚጠራው ወደ ሊቀ ካህናቱ ሂድ፤ ወደ ቤተ መቅደስ በሚያስገባው በር አጠገብ በየተራ ከሕዝቡ ገንዘብ የመሰብሰብ ኀላፊነት የተሰጣቸው ካህናት እስከ አሁን ምን ያኽል ገንዘብ እንደ ሰበሰቡ የሚገልጥ የሒሳብ ማስረጃ ይዘህ ና፤


ንጉሥ ኢዮአስ “የገንዘብ መሰብሰቢያ ሣጥን ሠርታችሁ በቤተ መቅደሱ ቅጽር በር በስተውጭ በኩል አኑሩት” ሲል ሌዋውያኑን አዘዘ፤