2 ዜና መዋዕል 22:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አካዝያስ ዕድሜው ኻያ ሁለት ዓመት ሲሆን ነገሠ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ገዛ፤ የንጉሥ አክዓብ ልጅ፥ የእስራኤል ንጉሥ የዖምሪ የልጅ ልጅ የሆነች ዐታልያ ተብላ የምትጠራ እናቱ ወደ ክፋት የሚመራ ምክር ትሰጠው ስለ ነበር አካዝያስ የንጉሥ አክዓብን መጥፎ ምሳሌነት ተከተለ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አካዝያስ ሲነግሥ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ጎቶልያ ትባላለች፤ እርሷም የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አካዝያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው አርባ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ጎቶሊያ የተባለች የዘንበሪ ልጅ ነበረች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አካዝያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው ሃያ ሁለት ዓመት ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ጎቶልያ የተባለች የዘንበሪ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አካዝያስም መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው አርባ ሁለት ዓመት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ጎቶሊያ የተባለች የዖምሪ ልጅ ነበረች። |
ሚስቱም የአክዓብ ልጅ ስለ ነበረች እንደ አክዓብ ቤተሰብ የእስራኤል ነገሥታት ይፈጽሙት የነበረውን የክፋት መንገድ ተከተለ፤ በደል በመሥራትም እግዚአብሔርን አሳዘነ፤
በነገሠም ጊዜ የኻያ ሁለት ዓመት ልጅ ነበረ፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ አንድ ዓመት ብቻ ገዛ፤ እናቱ ዐታልያ ተብላ የምትጠራው የአክዓብ ልጅ የእስራኤል ንጉሥ የነበረው የዖምሪ የልጅ ልጅ ነበረች።
ከአክዓብ ሴቶች ልጆች አንዲቱን በማግባቱ፥ የንጉሥ አክዓብንና የሌሎቹን የእስራኤል ነገሥታት መጥፎ ምሳሌነት ተከትሎ በእግዚአብሔር ፊት ኃጢአትን ሠራ፤
ዐረቦችና ተከታዮቻቸው ወረራ ባደረጉ ጊዜ በሰፈሩ ላይ አደጋ ጥለው ከሁሉ ታናሽ ከሆነው ከአካዝያስ በቀር የንጉሥ ኢዮራምን ወንዶች ልጆች በሙሉ ገደሉ፤ ስለዚህ የኢየሩሳሌም ሕዝብ አካዝያስ በአባቱ እግር ተተክቶ እንዲነግሥ አደረገ፤