ዳዊትም አምልጦ ሳሙኤል ወደነበረበት ወደ ራማ መጣ፤ ሳኦል ያደረገበትንም በደል ሁሉ ነገረው፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤልና ዳዊት በራማ ወደምትገኘው ወደ ናዮት ሄደው በዚያ ተቀመጡ፤
1 ሳሙኤል 19:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እርሱ ራሱ ወደ ራማ ለመሄድ ተነሣ፤ እዚያም ሴኩ በሚባለው ስፍራ ወደሚገኘው ወደ አንድ ታላቅ የውሃ ጒድጓድ በደረሰ ጊዜ “ሳሙኤልና ዳዊት የሚገኙት የት ነው?” ብሎ ቢጠይቅ፥ በናዮት መኖራቸው ተነገረው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በመጨረሻም፣ እርሱ ራሱ ወደ አርማቴም ሄደ፤ ከዚያም በሤኩ ወዳለው ትልቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ጕድጓድ እንደ ደረሰ፣ “ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ሲል ጠየቀ። አንድ ሰውም “በአርማቴም በምትገኘው በነዋት ዘራማ ናቸው” ብሎ ነገረው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመጨረሻም፥ እርሱ ራሱ ወደ ራማ ሄደ፤ ከዚያም በሴኩ ወዳለው ትልቅ የውሃ ማጠራቀሚያ ጉድጓድ እንደ ደረሰ፥ “ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ሲል ጠየቀ። አንድ ሰውም “በራማ በምትገኘው የራማዋ ናዮት ናቸው” ብሎ ነገረው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳኦልም እጅግ ተቈጣ፤ እርሱም ደግሞ ወደ አርማቴም መጣ፤ በመሴፋም አውድማ ወዳለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድጓድ ደረሰ። “ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው?” ብሎ ጠየቀ፤ “እነሆ፥ በአውቴዘራማ ናቸው” አሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሳኦልም ቁጣ ነደደ፥ እርሱም ደግሞ ወደ አርማቴም መጣ፥ በሤኩም ወዳለው ወደ ታላቁ የውኃ ጕድጓድ ደረሰ። ሳሙኤልና ዳዊት የት ናቸው? ብሎ ጠየቀ፥ አንድ ሰውም፦ እነሆ፥ በአርማቴም አገር በነዋትዘራማ ናቸው አለው። |
ዳዊትም አምልጦ ሳሙኤል ወደነበረበት ወደ ራማ መጣ፤ ሳኦል ያደረገበትንም በደል ሁሉ ነገረው፤ ከዚህም በኋላ ሳሙኤልና ዳዊት በራማ ወደምትገኘው ወደ ናዮት ሄደው በዚያ ተቀመጡ፤
ሳኦል ይህን በሰማ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም እንደዚያው ትንቢት መናገር ቀጠሉ፤ ሳኦልም ለሦስተኛ ጊዜ ሌሎች መልእክተኞችን ቢልክ ያው ነገር በእነርሱም ላይ ተደገመ፤