መጽሐፈ ጦቢት 7:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ኤቅባጥና ከተማ በገቡ ጊዜ ጦብያ “ወንድሜ አዛርያ በቀጥታ ወደ ወንድማችን ወደ ራጉኤል ቤት ውሰደኝ” አለው። እሱም ወደ ራጉኤል ቤት ወስደው፤ ራጉኤልም በግቢው አጥር በር አጠገብ ተቀምጦ አገኙት፤ እነርሱ አስቀድመው ሰላምታ አቀረቡለት። እርሱም “እንደምናችሁ ወንድሞቼ፥ እንኳን ደኀና መጣችሁ” አለና ወደ ቤቱ አስገባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ራጉኤልም ቤት ደረሱ፤ ሣራም ተቀብላ ደስ አሰኘቻቸው፤ እንዲሁ እነርሱም እርሷን ደስ አሰኙአት፤ ወደ ቤትም አስገባቻቸው። |