ወር ስሙን ከእርሷ ወረሰ፤ ወቅቷንም ጠብቃ ድንቅ መለዋወጥን ታሳያለች፤ በደመና ያሉ አእላፋት ዓርማ፤ በሰማያት ቅስትም ላይ ሆና የምታበራ ናት። ለከዋክብት
ጨረቃስ እንደ ስሟ ናት፤ ዕድገትዋም ድንቅ ነው፤ በሰማይ ሠራዊት ሥርዐትም ሕፀፅንና ምላትን ማፈራረቅዋ ድንቅ ነው፤ በሰማይ ሠራዊት መካከልም ታበራለች።