በምስጋናችሁ ጌታን አወድሱት፤ የምትችሉትንም ያህል ከፍ አድርጉት፤ እርሱ ግን ከዚያም የመጠቀ ነው። በምስጋና ወቅት ኃይላችሁን ሁሉ ተጠቀሙ፤ ሰውነታችሁ አይዛል፤ ከፍጻሜው ግን ከቶውንም አትደርሱም።
ጨርሳችሁ ማመስገንን አትጠነቅቁምና፤ የተቻላችሁን ያህል እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ እርሱ ግን ከዚህ ሁሉ በላይ ነው። በፍጹም ኀይላችሁም አግንኑት፤ አትደርሱበትምና እርሱን ማመስገንን ቸል አትበሉ።