ማለዳን ከሚጠብቁ የሌሊት ጠባቂዎች ይልቅ፥ ነፍሴ ጌታን ትጠብቃለች፥ ማለዳን ከሚጠብቁ ጠባቂዎች ይልቅ።
ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ አዎን፤ ዘብ ዐዳሪ ንጋትን ከሚጠባበቅ ይልቅ፣ ነፍሴ ጌታን ትጠባበቃለች።
ንጋትን ከሚጠባበቁ ጠባቂዎች ይልቅ እኔ እግዚአብሔርን በናፍቆት እጠባበቃለሁ።
ማለዳ ጮኽሁ፥ ቃልህንም ተስፋ አድርጌአለሁ።
የዕርገት መዝሙር። እነሆ፥ ጌታን ባርኩ፥ በአምላካችን ቤት አደባባዮች የምትቆሙ እናንተ የጌታ ባርያዎች ሁላችሁ።
አቤቱ አሁንስ ማንን እጠብቃለሁ? ተስፋዬ በአንተ ነው።።
ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች፥ ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ።
ያየውም፦ ጌታ ሆይ፥ ቀኑን ሁሉ ዘወትር በማማ ላይ ቆሜአለሁ፥ ሌሊቱንም ሁሉ በመጠበቂያዬ ላይ ተተክያለሁ፤
ድንጋያማም ወደ ሆነ ስፍራ እንዳይወድቁ ፈርተው፥ ከመርከቡ በስተ ኋላ አራት መልሕቅ አወረዱ፤ ቀንም እንዲሆን ተመኙ።