ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ጠቢብም ሁን፥ ልብህንም በቀናው መንገድ ምራ።
ልጄ ሆይ አድምጥ፤ ጠቢብም ሁን፤ ልብህም ከትክክለኛው መንገድ አይውጣ።
ልጄ ሆይ! አድምጥ፤ ብልኅም ሁን፥ ከእግዚአብሔርም መንገድ ፈቀቅ አትበል፤
ልጄ ሆይ፥ ስማ፥ ጠቢብም ሁን፥ የልብህንም ዐሳብ አቅና።
ልብህን ለምክር ስጥ፥ ጆሮህንም እንዲሁ ለእውቀት ቃላት።
ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዐይኖችህም መንገዴን ይውደዱ።
የእግርህን መንገድ አቅና፥ አካሄድህም ሁሉ ይጽና።
አንተ ሰነፍ፥ ወደ ገብረ ጉንዳን ሂድ፥ መንገድዋንም ተመልክተህ ጠቢብ ሁን።
አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።”
‘ይህ ልጃችን እልከኛና ዓመፀኛ ነው፤ አይታዘዘንም፤ አባካኝና ሰካራም ነው’ ብለው ለአለቆች ይንገሯቸው።
“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።