ምሳሌ 1:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በሙሉ ሕይወት እያሉ፥ ከነነፍሳቸው፥ እንደ ሲኦል ሆነን እንዋጣቸው፥ ወደ ጉድጓድ እንደሚወድቁም ይሁኑ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ መቃብር፣ ወደ ጕድጓድ እንደሚወርዱ፣ ከነሕይወታቸው በሙሉ እንዋጣቸው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቃብር ሙታንን እንደሚውጥ፥ እኛም እነርሱን በሕይወት ሳሉ እንዋጣቸው! ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱም ሰዎች እናድርጋቸው! የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሕይወት ሳለ እንደ ሲኦል እንዋጠው፥ መታሰቢያውንም ከምድር እናጥፋ፤ |
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር በላኝ፥ አደቀቀኝም፥ እንደ ባዶ ዕቃም አደረገኝ፥ እንደ ዘንዶም ዋጠኝ፥ ከሚጣፍጠውም ምግቤ ሆዱን ሞላ፥ እኔንም አውጥቶ ተፋኝ።
ዔ። ጠላቶችሽ ሁሉ አፋቸውን አላቀቁብሽ፥ እያፍዋጩና ጥርሳቸውን እያፋጩ፦ ውጠናታል፥ ነገር ግን ተስፋ ያደረግናት ቀን ይህች ናት፥ አግኝተናታል አይተናትማል ይላሉ።
ያም ወገን በሞተ ጊዜ፥ እሳቲቱም ሁለት መቶ ኀምሳውን ሰዎች ባቃጠለች ጊዜ ምድሪቱ አፍዋን ከፍታ እነርሱን ከቆሬ ጋር ዋጠቻቸው፤ እነርሱም ለምልክት ሆኑ።