ዘኍል 23:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላቅም ምድረ በዳውን ከላይ ወደሚመለከተው ወደ ፌጎር ራስ ላይ በለዓምን ወሰደው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ባላቅም በለዓምን ምድረ በዳው ቍልቍል ወደሚታይበት ወደ ፌጎር ጫፍ አወጣው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ባላቅ በለዓምን በበረሓው ትይዩ ወዳለው ወደ ፔዖር ተራራ ጫፍ ላይ ይዞት ወጣ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም በለዓምን በምድረ በዳ ወደ ተከበበው ወደ ፌጎር ተራራ ወሰደው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም ምድረ በዳውን ከላይ ወደሚመለከተው ወደ ፌጎር ላይ በለዓምን ወሰደው። |
ባላቅም በለዓምን እንዲህ አለው፦ “እባክህ ና፥ ወደ ሌላ ስፍራ እወስድሃለሁ፤ ምናልባት በዚህ ሆነህ እነርሱን ብትረግምልኝ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝ ይሆናል።”
በለዓምም ጌታ እስራኤልን መባረክ ደስ እንደሚያሰኘው ባየ ጊዜ፥ አስቀድሞ ያደርግ የነበረውን አስማት ለመሻት አልሄደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን አቀና።