ዘኍል 23:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ባላቅም በለዓምን፦ “ከቶ አትርገማቸው፥ ከቶም አትባርካቸው” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ባላቅ በለዓምን፣ “እንግዲያውስ ፈጽሞ አትርገማቸው፤ ፈጽሞም አትመርቃቸው!” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ባላቅ በለዓምን “መቼም የእስራኤልን ሕዝብ ለመርገም እምቢ ብለሃል፤ ባይሆን እንኳ አትመርቃቸው!” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላቅም በለዓምን አለው፥ “ከቶ አትርገማቸው፤ ከቶም አትባርካቸው።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባላቅም በለዓምን፦ ከቶ አትርገማቸው፥ ከቶም አትባርካቸው አለው። |