ማርቆስ 5:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢየሱስም አብሮት ሄደ። ብዙ ሕዝብም እያጨናነቀው ተከተለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢየሱስም ዐብሮት ሄደ። ብዙ ሕዝብም ዙሪያውን እያጨናነቀው ተከተለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም አብሮት ሄደ፤ ብዙ ሰዎችም ተከትለውት በዙሪያው ያጣብቡት ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም ጋር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት አጋፉትም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም ጋር ሄደ። ብዙ ሕዝብም ተከተሉት አጋፉትም። |
ሕዝብም በብዛት እየተሰበሰቡ በነበሩ ጊዜ እንዲህ ይል ጀመር፦ “ይህ ትውልድ ክፉ ትውልድ ነው፤ ምልክትን ይፈልጋል፤ ከዮናስም ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም።
በዚያን ጊዜ፥ በሺዎች የሚቈጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ከብዛታቸው የተነሣ እየተረጋገጡ ሳለ፥ በቅድሚያ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ይል ጀመር፦ ከፈሪሳውያን እርሾ ተጠንቀቁ፤ እርሱም ግብዝነት ነው።
ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ሄደ። ወደ ቤቱም በቀረበ ጊዜ መቶ አለቃው ወዳጆቹን ወደ እርሱ ልኮ እንዲህ አለው፦ “ጌታ ሆይ! ከቤቴ ጣራ በታች ልትገባ አይገባኝምና ራስህን አታድክም፤
ዐሥራ ሁለት ዓመት የሚሆናት አንዲት ሴት ልጅ ነበረችውና፤ እርሷም ለመሞት እያጣጣረች ነበር። ሲሄድም ሕዝቡ በዙርያው እየተጋፉት ያጨናንቁት ነበር።
እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፤ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፤ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፤