ሉቃስ 2:44 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ከመንገደኞች ጋር የነበረ መስሏቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፤ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም መካከል ፈለጉት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዐብሯቸው ያለ መስሏቸው የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙ፤ በኋላ ግን ከዘመዶቻቸውና ከወዳጆቻቸው ዘንድ ይፈልጉት ጀመር፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመንገደኞች ጋር አብሮ የሚሄድ መስሎአቸው የአንድ ቀን መንገድ ሲጓዙ ዋሉ፤ ከዚያም በኋላ ከዘመዶቻቸውና ከሚያውቋቸው ሰዎች ዘንድ ይፈልጉት ጀመር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንገድም ከሰዎች ጋር ያለ መስሎአቸው ነበር፤ ያንድ ቀን መንገድንም ከሄዱ በኋላ ዕለቱን ከዘመዶቹ፥ ከሚያውቁትም ዘንድ ፈለጉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመንገደኞች ጋር የነበረ ስለ መሰላቸው የአንድ ቀን መንገድ ሄዱ፥ ከዘመዶቻቸውም ከሚያውቋቸውም ዘንድ ፈለጉት፤ |
ብዙ ሕዝቦችም መጥተው እንዲህ ይላሉ፤ “ኑ፤ ወደ ጌታ ተራራ፤ ወደ ያዕቆብ አምላክ ቤት እንውጣ፤ እርሱ መንገዱን ያስተምረናል፤ በጎዳናውም እንሄዳለን።” ሕግ ከጽዮን፤ የእግዚአብሔር ቃል ከኢየሩሳሌም ይወጣልና።